African news reported our election campaigning platform

  • Home
  • Product
  • African news reported our election campaigning platform

ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ የሚረዳ “ምርጫዬ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ !ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዲሁም ፓርቲዎች ሀሳባቸውን ለህዝቡ እንዲሸጡ የሚያስችል ምርጫዬ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያና ድረ ገጽ ማዘጋጀቱን እውነት ኮሚኒኬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

በአሁኑ ወቅት መራጮች ስለሚመርጡት ፓርቲ እና ተመራጭ የመረጃ ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ይህንን ፍላጎት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ መሸፈን ይቻል ዘንድ ይህ መተግበሪያና ድረ-ገጽ መዘጋጀቱ ነው ያስታወቁት።በተለይ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳዎችን ለማድረግ ቴክኖሎጂውን እንደ ትልቅ አቅም መጠቀም እንደሚገባ የጠቀሱት አዘጋጆቹ ሁሉንም ፓርቲ ያለምንም ክፍያ በእኩል ለማሳተፍ የሚያስችል መድረክ መመቻቸቱንም ጠቁመዋል።

በምርጫ መተግበሪያው/ ድረ ገጹ ላይ የፓርቲዎች መግለጫ፣የሲቪክ ማህበራት እና የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድ መረጃ፣ ለፓርቲዎች ድጋፍ የሚደረግበት የእርዳታ ወይም የልገሳ ፎርም፤ ሰነዶች እና ተቀሳቃሽ ምስሎች ማጋሪያ፣ ዜና፣ ወደ ማህበራዊ ገጽ ማጋሪያ እንዲሁም ኩነቶችን ማስተዋወቂያ በውስጡ አካቷል።

እውነት ኮሚኒኬሽን ኃ/የ/የግ/ማኅበር በወጣቶች የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን ይህንን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን፤ በተለይ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን አስመልክቶ በሙያቸው በበጎ ፈቃደኝነት ሥራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።

ወደፊት ትልልቅ ለውጥ የሚፈጥሩ የቴከኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ገቢያው ለማምጣት በሂደት ላይ እንደሚገኙ ገልጸውልናል።

1 Comment

  • Riva Collins

    November 9, 2019 - 2:09 am

    It’s no secret that the digital industry is booming. From exciting startups to need ghor hmiu global and brands, companies are reaching out.

Leave A Comment

An emerging technology and branding company that strives to make a better Africa via technology and Innovation.

Addis Ababa, Ethiopia
(Mon- Saturday)
(8am - 05 pm)
X